የሐራጅ‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ ሽያጭ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

በአፈ ከሳሽ ዶ/ር ሃይሉ በላይ ፡ በኣፈ/ ተከሳሽ ወ/ሮ አልማዝ በየነ መካከል ባለው የአፈጻጸም ክርክር ጉዳይ በመቐለ ከተማ ፣ ሰሜን ክ/ከተማ፣ ሰውሒ ንጉስ ቀበሌ ክልል ውስጥ ከመነን ሆቴል ጎን የሚገኝ በካርታ ቁጥር 01/ 1111 በወ/ሮ አልማዝ በየነ ሥም የሚታወቅ በምስራት መንገድ በምእራብ ሃለቃ አይነኩሉ በሰሜን ወ/ማርያም በደቡብ ወ/ሮ ብዙ የሚዋሰን 275.93 ካሬሜትር ውስጥ የሰፈረ ቤትና ቦታ በመነሻ ዋጋ ብር 7,738,478.76 ( ሰባት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ አራት መቶ ሰባ ስምንት ብር 76/100) በ24/4/2017 ዓ.ም ከ3፡00 ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ እስከ 6፡00 በግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ እንዲሸጥ የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል። ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ካርድ በመያዝ በተገለጸው ቤትና ቦታ ቀንና ሰዓት ተገኝታችሁ ለመጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ያሸነፈ ያሸነፈበትን ዋጋ 25% በሞ/85 ወዲያውኑ በማስያዝ የቀረውን ደግሞ በአስር ቀን ውስጥ የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆኑን ፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት