መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ

ለምርት አገልግሎት የሚውል ውስጥ ድንጋይ ከሰል አወዳድሮ ለመግዛት የወጣ ግልፅ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት ጠቅላላ ከምንጠቀምበት 85,000 ሜትሪክ ቶን የታጠበ 105,000 ሜትሪክ ቶን ያልታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱን መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አዲስ አበባ ስታድ ም ወጋገን ህንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ወይም መቐለ ዋና መስራቤት በአካል በመገኘት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፣

  1. በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው የሚሳተፉ ድርጅቶች የከሰል ድንጋይ በማምረት በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸው የሚገልፅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው፣ የመዐድን ፈቃድና የመሬት ይዞታ ሰርተፊኬት የሚግልጽ ማስረጃ ከጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የታጠበ የድንጋይ ከሰል ለሚያቀርቡ ደግሞ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ባለቤት መሆናቸውና የስራ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 1,000,000 (አንድ ሚልዮን ብር) በመሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ ለብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱን ከላይ በተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሱት ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ የድርጅታቸውን አርማና ማህተም ያለው ደብዳቤ በመፃፍ ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከዚህ ግልጽ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ጋር አብሮ ከተገለፀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ያቀርቡትን የሃገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (የታጠበ/ያልታጠበ በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ቀን ወይም ከዛ በፊት በራሳቸው ወጪ ለምርመራ ናሙና (ሳምፕል) ቢያንስ 10 ኪ.ግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ (ናሙናው የሚቀርበው መቀሌ በሚገኘው ዋና ፋብሪካ ይሆናል)
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውና በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱት ሰነዶችና በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ናሙና (ሳምፕል) እስከ መስከረም 07/ 2017 ከሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዳቸው መቀሌ በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ቁጥር 15 ስለሚገኝ የግዥና አቅርቦት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በእለቱ መስከረም 07/ 2017 ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱን የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን
  8. ፋብሪካው ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር

+251 34 440 5806/+251 912 502 596/

+251 914 729 516 ወይም procurementmessebocement2020@gmail.com መጠቀም ይቻላል፡፡

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ኃ.የተ.የግ/ማህበር