የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ቁጥር ት/ክ/ኤ/አ/011/2015

የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ጐማዎች፣ ባትሪዎችና እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው።

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነትና መጠን

ብዛት

ሎት 1

የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች ጐማ ከነካላማደሪያውና ፍላፕ እንዲሁም ራድያል ጐማ (7.50x16 ፣ 7.00x16 ፣ 8.25x17 ፣12.00x20 ፣ 10.00x20)

978

ሎት 2

የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪዎች ባትሪ (12V/150A ፣ 12V/120A ፣ 12V/70A)

88

ሎት 3

የተለያዩ ዓይነት የተሽከርካሪ ዕቃዎች /ፊልትሮዎች/ ብሬክ ፓድ እና ብሬክ ሹ

1411

  1. በጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑ ግብር የተፈከለበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. አድራሻ፡- መቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ ቤት 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 31፣
  4. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሎት ı እና ለሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት የገንዘብ መጠን ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ በትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ ቁጥር ምልክት በማድረግ ት/ክ/ኤ/አ/011/2015 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት‍‍‍‍‌‍‌‍‌‌‌‍‍‍‌‍ ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 31 ለዚሁ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል
  7. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‏‏‎‏‎‏‎‎‎‏‏‏‎‏ውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-34 240 6712 መደወል ይችላሉ።

የትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት