የካፍቴሪያ አገልግሎት ተቋራጭ የጨረታ ሠነድ
የጨረታ ቁጥር - Service 0001/2016
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንደስትሪ አ/ማህበር አዲስ አበባ /ሰሚት፣ ንፋስ ስልክና ተክለሃይማኖት/ ' ሃዋሳ፣ መቀሌና ደሴ በሚገኙ ፋብሪካዎቹ ለሠራተኞቹ የ24 ሠዓት የምግብና የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋራጭ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በሥራው ልምድ ያላቸው ተቋራጮች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ከዚህ በታች የቀረቡትን ዝርዝር የጨረታ ሠነዶችን በማሟላት እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፣
2. በጨረታው የሚሳተፍ ድርጅት ለክበቡ የምግብ እና መጠጥ ግብዓቶችን ለማመላለሻ የሚሆን ቢያንስ አንድ መለስተኛ የመጫን አቅም ያለው ተሽከርካሪ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህንኑ የሚያሳይ የሥራ መኪና ሊብሬ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. በጨረታ የሚያሸንፍ ድርጅት ሥራውን በተገቢው ለመምራት የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑን ለማየት ከሁለት ወር በኋላ የሚመለስ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
4. በጨረታው የሚሳተፍ ድርጅት ከዚህ ቀደም በቀን ለ24 ሰዓት እና በሦስት ፈረቃ ከሚያመርት ፋብሪካ ጋር ተመሳሳይ የምግብና መጠጥ አቅርቢት ሥራ ላይ በመሳተፍ መልካም ተሞክሮ ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ የሥራ ልምድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. በጨረታው የሚሳተፍ ድርጅት 30.000.00 (ሰላሳ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. አንድ ድርጅት ከአንድ ፋብሪካ በላይ የካፊቴሪያ አገልግሎት ለመስጠት መጫረት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ፋብሪካ በላይ አገልግሎት ለመስጠት ከተጫረተ ለእያንዳንዱ ጨረታ ከላይ በተራ ቁጥር 3 እና 5 ያሉትን በተናጠል CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ ህጋዊ መብት አለው፡፡ አድራሻ፡-
1. አዲስ አበባ ለሚገኙ ፋብሪካዎች የሚጫረቱ ተጫራጮች አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሽገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንፃ ሦስተኛ ፎቅ - ቢሮ ቁጥር 002 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡45 ድረስ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፕሮፖሳላቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተለያየ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
2. መቀሌ፣ ሃዋሳና ደሴ ለሚገኙ ፋብሪካዎች የሚጫረቱ ተጫራጮች ፋብሪካዎቹ ባሉበት ቅጥር ግቢ በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡45 ድረስ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፕሮፖሳላቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተለያየ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡