- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ ከዋናው መ/ቤት መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንጻ ፋይናንስ መምሪያ 5ተኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ በመክፈል መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ/ም መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ/ም 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ሰዓት በአ/ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸለት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ተሽከርካሪውን ማንሳት አለበት፡፡ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ካላነሱ የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለአ/ማህበሩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ለ2ተኛ አሸናፊ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- የተሽከርካሪውን የስም ዝውውርና ህግ የሚጠይቃቸውን ማንኛውም ክፍያዎች (ወጪዎች) አሸናፊ የሚሸፍን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ዮሴፍ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የአ/ማህበሩ ጋራዥ በመገኘት አውቶቢሶቹን በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫራቻ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 09-14-70-38-08 ወይም 011 4 70 83 32 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፤