የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቀሌ ዲስትሪክት ለኪዳነ ተክሉ እና ዘርኡ አብረሃ አትክልትና ፍራፍሬ እርሻ ልማት ሕ/ሽ/ማሕበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዘውንና በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 98/90 እና 216/92 መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው ስም

የሚሸጠው ንብረት አይነት

ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ

ጨረታ ደረጃ

የድርድር ጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር)

ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት

ኪዳነ ተክሉ እና ዘርኡ ኣብርሃ ሕ/ሽ/ማህበር

ሞዴል NPR71፣35 ኩንታል የሚጭን አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ

የመጀመሪያ

590,000.00

ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት- 6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ:

  1. 1. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት አይነት የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ሶስተኛውን ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. 2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  3. 3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በመቀሌ ዲስትሪክት ይካሄዳል፡፡
  4. 4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  5. 5. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ በ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን ሲኖርበት፣ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
  6. 6. 15% /አስራ አምስት/ በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል ይኖርበታል፡፡
  7. 7. አሸናፊው ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት ከፈለገ የባንኩን ብድር መስፈርት ማሟላትና ቢያንስ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል፡፡
  8. 8. የስም ማዛወሪያና በሽያጭ ምክንያት የሚፈለግ ማንኛውንም የመንግሥት ክፍያዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል፡፡
  9. 9. ስለ ንብረቱ ዝርዝር ሁኔታ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት በሚገኘው የፕሮጀክት ማስታመሚያና ብድር ማገገሚያ ቡድን በግንባር በመቅረብ ወይመ በስልከ ቁጥር 0344-419016 ወይመ 0344-407439 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
  10. 10. ንብረቱን መመልከት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በግንባር ቀርቦ መመልከት ይቻላል፡፡
  11. 11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐስ ዲስትሪክት