ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን 23/4/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : በየሎቱ የተለያየ ነዉ ( በ31 ኛዉ እና 16ኛዉ ነዉ)
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : : በየሎቱ የተለያየ ነዉ (በ31 ኛዉ እና 16ኛዉ ነዉ)
ድብ | የእቃው | የጨረታ | የጨረታ | ጨረታው | ጨረታው | ||
ቀን | ሰዓት | ቀን | ሰዓት | ||||
ምድብ 1 | ለኢንጅነሪንግ | 120,000 | ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተየባንክ ዋስትና ከዋጋ ሰነድ ጋርየሚቀርብ | በ31 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ31 ኛው ቀን | 3፡30 |
ምድብ 2 | የሞተር ሳይክል ግዢ | 120,000 | በ31 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ31 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 3 | የትራክተር ግዢ | 120,000 | በ31 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ31 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 4 | የሠራተኞች | 50,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 5 | የማገዶ | 50,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 6 | የስፖርት | 20,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 7 | የቢሮ መጋረጃና | 50,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 8 | የመኪና | 20,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 | |
ምድብ 9 | የአትክልት | 50,000 | በ16 ኛው ቀን | 3፡00 ሰዓት | በ16 ኛው ቀን | 3፡30 |
ራያ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሰንጠረዡ የተመለከተውን ምድብ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባችሁ፡፡
- 1. ተጫራቾች የ2012 ዓ.ም ህጋዊ ለየምድቡ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጊዜው ያላለፈበት የተሰጠ የምስክር ወረቀት ወይም ታክስ ከሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይታቸው በእቃ/በአገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
- 2. ተጫራቾች ከምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ያሉት የጨረታ ሰነድ መሸጫ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ ሲሆን ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ደግሞ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 31 ቀናት ከምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ላሉት ሲሆን ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ደግሞ ለተከታታይ 15 ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- 3. ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለምድብ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት እና አራት እንዲሁም ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ላሉት ደግሞ አንድ ፋይናንሺያል ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት በ31ኛው ቀን ከምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ላሉት ሲሆን ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ደግሞ በ16ኛው ፤ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ስዓት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተመለከተው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 4. ጨረታው በ31ኛው ቀን ከምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ላሉት ሲሆን ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ደግሞ በ 16ኛው ቀን ልከ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ውስጥ በግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አድሚን ህንፃ ቁጥር 5 ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ይከፈታል ነገር ግን 16ኛው ቀን ወይም 31ኛው ቀን ሃይማኖታዊ ወይም መንግስታዊ በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 120 ከምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ላሉት ሲሆን ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ እና 90 ቀናት ይሆናል፡፡
- 6. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀባንክ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼክ ወይምየባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ከሬዲት በቴክኒካል ፖስታ ታሽጎ ለምድብ አንድ እስከ ምድብ ሦስት ብቻ መቅረብ ሲኖርባቸው ከምድብ አራት እስከ ምድብ ዘጠኝ ላሉት ደግሞ በፋይናንሽያል ክፍሉ ላይ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- 7. አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ራያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- 8. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ www.rayu.org ወይም በስልክ ቁጥር 03 42 47 29 27/03 42 47 83 75 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
ራያ ዩኒቨርሲቲ