በኢትዩጰያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የኢትዩጽያ ምርጥ ዘር ኣቅርቦት ትግራይ ማእከል

የሰራተኞች ሰርቪስ ጨረታ ማስታወቅያ

ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መቐለ ቅርንጫፍ ሰራተኞች ሰርቪስ ኮስተር መኪና በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በቅ/ጽ/ቤቱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ጨረታው 13/08/2018ዓ.ም ከሰዓት በፊት 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 3፡15 ሰዓት በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፈታል። ስለዚህ የኪራይ አፈጻጸሙ በጨረታ ሠነዱ በተገለፀው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን እየገለጽን፣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋውን 5% በሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በሚቀጥለው አድራሻ መጠቀም ይቻላል።

አድራሻ

ሓሚዳይ ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ፋብሪካ ፊት ለፊት