የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር TG/AGP-CU
10/2011
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከግብርና ዕድገት ፕሮግራም (AGP-II) በተገኘ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፡-
- ሎት 1. የአይቲ ዕቃዎች (IT Equipments)
- ሎት 2. ኤሌክትሪክ ጀነሬተርና አነስተኛ የእጅ መሣሪያዎች
- ሎት 3. የእንሰሳት ሕክምና መገልገያ ዕቃዎች
- ሎት 4. የማንጎና የአቮካዶ ፍሬ
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑምበጨረታውላይለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን የተዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብ/ በመክፈል ከታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከቢሮአችን የዕቃ ግዢ ንዑስ ሥራ ሂደት በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በጨረታዉ ላይ ለመሳተፍ ቀጥለዉ የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሠርተፊኬት፣የቫት ሰርተፈኬት፣ ያለፈዉ ወር ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደርአለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተገለፀዉን መጠን በቢሯችን ስም በሲፒኦ አሠርተዉ ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 15% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያዉ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ንኡስ ሥራ ሂደት ይከፈታል፡፡
- ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0344-403663፣ 0344-404723 ወይም በፋክስ ቁጥር 0344-409971 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ
ድሕሪት